ድንግልናዬስ?

ድንግልናዬስ?

ድንግልናዬስ

ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ሰማዩ ጨፍግጎ በደመና ቢታጠርም ልቤ ግን በደስታ ጮቤ እየረገጠች ነው፡፡የአየሩ ቅዝቃዜ  ቢያንዘፈዝፍም ውስጤ ግን በሙቀት ተጥለቅልቋል፡፡ምክንያቱም ዛሬ  የእኔ ቀን ነች ፡፡የደስታ ሙዚቃ የፈንጠዚያ ዝማሬ የምዘምርባት ቀኔ…..፡፡ወደ አዲስ የህይወት ምዕራፍ የምሸጋገርበት፤ሙሉ ሰው ፤ሙሉ ሴት የምሆንባት የተቀደሰች የፍቅር ሀዲዴ፡፡

ይህቺን የዛሬዋን ቀን ክርስቲያኖች የክርስቶስን ዳግም መምጣት የሚናፍቁትን ያህል ናፍቄ..ጦርነት  የዘመተባት ልጇ በህይወት ተርፎ መመለሱን እንደምትናፍቅ እናት ለዓመታት ጠብቄ ያገኘዋት ቀኔ ነች፡፡ሴት የምሆንባት ቀን ..እንቡጥነቴ ፈንድቶ ወደ አበባነት የምሸጋገርበት ልዩ ቀኔ ነች፡፡ከአንዱ የህይወት እርከን ወደ ሌላው የምሸጋገርባት ከወርቅ የተሰራች የህይወት ድልድዬ፡፡

መኝታ  ቤቱ በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቷል፡፡፡አራቱም ኮሪደሮች ጥግ በተቀመጡ  አይንን በሚማርኩ ማስቀመጫዎች  ላይ የተሰኩ ነጫጭ ሻማዎች ተለኩሰው ከፍቅር ጋር የተለወሰ፤ከጉጉት ጋር የተቀየጠ የናፍቆት ብርሀን ይረጫሉ፡፡ከቴፑ አንደበት እየተስፈነጠረ የሚወጣው የዘሪቱ ከበደ ቄንጣዊ ዜማ ውስጥን ይነዝራል፡፡የመኝታ ቤቱ  ወለል የለበሰው ነጭ ምንጣፍ እላዩ ላይ ሮዝ እና ቀይ አበባ ተበትኖበት የሆነ የገነት አፀድ መስሏል፡፡

እኔና ፍቅረኛዬ በጣም ተጠጋግተን ጎን ለጎን አልጋው መሀል ቁጭ ብለናል፡፡ልቤ ደም መርጨቷን አቁማ ስጋት ነው እየተፋች ያለችው….ጉጉት ነው  በውስጧ የሚርመሰምሰባት..ፍትወት ነው የሚራወጥባት…. ፡፡በአጠቃላይ የምተነፍሰው አየር እያጠረኝ ነው…ሰውነቴ ብርክ ይዞት እየተንዘፈዘፍኩ ነው፡፡..ይሄ በእኔ ላይ ብቻ የተከሰተ የስሜት ነውጥ ነው ወይስ ሁሏም ልጃገረድ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኞ ላይ የሚከሰት የሄዋን ልጆች ሁሉ እጣ ይሆን  ..…? ምን እንደዚህ እንደሚያደርገኝ አላውቅም…:: የመጣውት  ፈልጌ እና ቋምጬ ነው ፡፡ግን ደግሞ ፈርቼያለው…. ደንግጬያለው… ጎጉቼያለው….ተስገብግቤያለው… ተንቀጥቅጬያለው….ተሸብሬያለው ….እንዴት እንዴት እያደረገኝ እንዳለም ለማወቅ ግራ ተጋብቼያለው፡፡

ለጊዜው እሱ ምን እየተሰማው እንዳለ መገመት አልችልም ፤ግን በመጠኑ የፈራ ይመስለኛል፡፡ቢሆንም እስከዛሬ ያካበተውን ልምድ ተጠቅሞ ሊያቀልጠኝ…ሊያሟሟኝ መወሰኑን አይን ውሀውን አይቼ ተረድቼየለው እና  ያንንም በመረዳቴ በደስታ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡እጁን አንስቶ ተከሻዬ ላይ ጣል አደረው…ቀጠለ ፡፡ወደ ታች ዝቅ አደረጋቸውና ጡቶቼን  ጨመቅ ጨመቅ ያደርጋቸው ጀመር..አጨማመቁ የሆነ የፒያኖ ቁልፎችን  በጥበብ የሚነካካ ሙዚቃ ከያኒ ያስመስለዋል……፡፡

ቀጠለ ጉንጮቼን ደጋግሞ ሳማቸው…..አንገቴ ስር ሳመኝ ….፡፡ እንደውም ላሰኝ ማለት ይቀላል…..፡፡.እናንተዬ አንገት እና ጆሮ አካባቢ መሳም እንዴ ነው እንዲህ ፍስስ የሚያደርገው..?ሲስመኝ ከትንፋሹ የሚወጣው  ሙቀት ወደ ጆሮዬ ሰርጎ ወደ አዕምሮዬ ሲበታተን ይታወቀኛል…ተበትኖም ልክ እንደማሪዋና እያደነዘዘኝ ነው…፡፡

ለመሆኑ እኔስ ምን እያደረግኩ ነው.?እየሳምኩት ይሆን .?ማወቅ አልቻልኩም…. ከንፈሬ ተነቅሎ አንገቴ አካባቢ እና ጆሮዬ ላይ የተለጠፈ መስሎኝ ነበር… ከንፈሬ ቦታው ላይ መሆኑን ያረጋገጥኩት የውዴ ከንፈር  መጥቶ ሲጣበቅባቸው ነው፡፡ መጠጠኝ… እስክቃትት መጠጠኝ፡፡

በስተመጨረሻ   እግሩ እንደተሰበረ ወንበር ወደ ኃላችን ተያይዘን ተገነደስን፡፡ሰውነቴ እቶን እሳት ውስጥ የተጣለ መስሎ ተሰማኝ….የትኛው ተራዳኢ መላአክ ክንፉን አርገብግቦ በመምጣት ከዚህ ቃጠሎ መንጥቆ ያወጣኝ ይሆን…..?ልቤም አቅም እያነሳት፤እየቀላለጠች  እና እየተልፈሰፈሰች  እንደመጣ እየታወቀኝ ነው፡፡እጅ እየሰጠውና ሙሉ በሙሉ እየተረታው ነው….

ልብሳችንን በምን ፍጥነትና ብርታት አወላልቀን እርቃን እንደቀረን ፍፅም ትዝ አይለኝም፡፡ሰውነቴ ከሰውነቱ ሲጣበቅ…እግሮቼን ፈልቅቆ ጭኔ ውስጥ ሲመሰግ ….እንደፌዴራል ዱላ የገረረ እንትኑ  ያለርህራሄ ትንሽ እንኰዋን ሳያባብለኝ  እየሰነጣጠቀኝ፤ እየከፋፈተኝ ወደ ውስጠቴ  ሲገባ በስልብታ ይታወቀኛል፡፡ …የሆነ አዲስ አይነት ጣዕም.. አዲስ አይነት ስቃይ… አዲስ አይነት ደስታ ተሰማኝ…፡፡ሚገርም ነው!!! ስቃይና ደስታ እንዲህ ይደባላለቃል …..?ለቅሶና ሳቅ እነዲህ ይዋሀዳል..?ማቃተት እና ማስካካት እንዲህ ተቀይጦ ሰማያዊ በሆነ የሙዚቃ ዜማ ይሰማል….?በቃ ለዘላለም በዛው ብጠፋ ተመኘው…፡፡ሰማየ ሰማያት ተንሳፍፌ…ከአንድ ፕላኔት ወደሌላው ፕላኔት ተስፈንጥሬ ተንሸራሸርኩ፡፡ለመሆን አሁን ካለንበት ምድር ጁፒተር ድረስ ለመጓዝ ስንት የብርሀን አመት ይፈጃል…..?እንዲያ ሩሩሩሩሩሩሩሩረቅ ከሆነ  ታዲያ በዚህች ሽራፊ ሰከንድ  በምን አይነት አስማታዊ ተአምር ደርሼ መጣው…..?

ወይ ጉዴ.. አዎ! የእውነት ፈጽሞ ወደ ትነትነት ተቀይሬ ከደመናው ጋር ልዋሀድ ሳይሆን አይቀርም…ወይንም ወደ ፈሳሽነት ተቀይሬ  እግዜሩ ያዘነበው ዝናብ ከፈጠረው ጎርፍ ጋር ተቀላቅዬ ልፈስም የተዘጋጀው ይመስለኛል  ……

የፍቅረኛዬ ጉልበት የአውሬ እየሆነ ነው…..የ17 ዓመት ያልፀኑ አጥንቶቼን እያደቀቃቸው ነው…ሰውነቴ እየተተረተረ…እየተበታተነ እየመሰለኝ ነው..፡፡ትንፋሼ ተቋርጣ ከምድራዊው ወደ ዘላለማዊው ዓለም ልትሸጋገር  የሽርፍራፊ ሰከንድ ያህል ጊዜ ሲቀራት  ጀግናዬ ተልዕኮውን ከፍጻሜ አድርሶ በመዝለፍለፍ ከጐኔ ተዘረረ፡፡ግዳዩን በብቃት እንደጣለ አዳኝ….እኔም አዳኚ በብቃቱና በጥንካሬው የዘረራት ሚስኪን ቀበሮ አድርጌ እራሴን በመሳል  ከደስታ እና ስቃይ ተቀይጦ የተመረተ እንባዬን  ወደ ውጭ በዝምታ አንጠባጠብኩ………………………………. ›››.…

ከአምስት ደቂቃዎች የዝምታ እና የተመስጦ እረፍት ቡኃላ ፍቅሬን እተጋደመበት ትቼው እየተንሻፈፍኩ እና እየተንቀጠቀጥኩ ሻወር ልወስድ ወደ ባኞ ቤት በመጎተት ገባው፡፡በቃ ይሄው ነው…ለአመታት የተንቀባረርኩበት..ለዘመናት የጎረርኩበት በቃ ይሄው ነው ….? ፡፡

ዋጋው ግን ለምንድነበር እንደዛ ገዝፎ ይታየኝ የነበረው….?የእውነት የማስበውን ያህል ዋጋ ኖርት ከሆነ እንዴት እንዲህ በአጭሩ ወደአለመኖር ሊሸጋገር ቻለ….?ለምን እምቢኝ ብሎ ለሳምንታት አልቆየም..እሺ ሳምንት ይቅር አንድ ቀን ..ይሁን እሺ አንድ ሰዓት..ሶስት አራት ሙከራ ድረስ ለማሰቸገር የሚያስችል ጥንካሬ እንዴት ያጣል….?ብጥቅ የሚለው ከሶፍት ነው እንዴ የሚሰራው…..?ነው ወይስ  ውዴ የወንዶች  ወንድ ስለሆነ ነው….? ፡፡

………ብቻ እንኰዋንም የእኔ ሆነ እንኰዋንም የእሱ ሆንኩ….

                     ›››››››››››››››››››››››››››››››

ከአስር ደቂቃዎች ቡኃላ በወሲብ ሙቀት ወርዝቶ የነበረ ገላዬን በቀዝቃዛ ውሃ አረስርሼ ስመለስ መኝታ ቤቱ ባዶ ነበር፡፡‹‹ጀግናዬ ወዴት ነህ .?››ብዬ ጠየቅኩ …በአንደበቴ ቃል አይደለም በልቤ መቃተት እንጂ….መልስ ከማግኘቴ በፊት  ከአልጋው ጠርዝ አካባቢ  ድንገት አንድ የወረቀት ቁራጭ አይኔ ውስጥ ገባ… አነሳውተት …፡፡የፍቅሬ የእጅ ፅሁፍ ነው፡፡በእዚህ ውብ  እጅ ፅሁፍ ምን አይነት የፍቅር ቅኔ ይሆን የተቀኘልኝ…..?ምን  አይነት ወዳሴ ድርሰት ይሆን የደረሰልኝ…….?ማንበብ ጀመርኩ……፡፡

****

የተረገምሽ ነሽ…ሁለት ዓመት ሙሉ ዋሸሺኝ…አንቺ የፍቅር ነጋዴ ነሽ….ለዛውም ቸርቻሪ…፡፡አስፓልት ጠርዝ ላይ እርቃንሽን የመብራት ፖል ተደግፈሽ ፍቅርን የምትነግጂ የሀጢያት ባለሟል፡፡ይገርማል በፍቅራችን ቆመርሽበት፡፡ልጃገረድ ነኝ ብለሽ ስታጃጅይኝና ስታሾፊብኝ ከረምሽ፡፡

አሁን ማድረግ ምችለውም.፤ የምፈልገውም ነገር አንቺን መርሳት ነው..፡፡ዝም ብሎ መርሳት….፡፡ምክንያቱም እኔ አንቺን አይደለውም…… አልደበድብሽም፤አልበቀልሽም…፡፡

ለማንኛውም አሁን  ልጠጣ ሄጄያለው፡፡በፈጠረሽ… ስመለስ እቤቴ እንዳላገኝሽ…ካገኘውሽ ግን ውሳኔዬን መልሼ ላጤን እችላለው ..እንደዛ ከሆነ ደግሞ ምን አልባት እገድልሽ ይሆናል፡፡…አየሽ እኔ የቤት ሸርሙጦችን በጣም  ነው  የምፀየፈው፡፡

******

 

አንብቤ ስጨርስ አጥወለወለኝ ፡፡በደስተታ ተንተርክኮ የነበረው ልቤ ከመቅፅበት ኩምትርትር አለ፡፡እርክት ብሎ የነበረው ስሜቴ መልሶ ሙሽሽ አለ፡፡ግራ ገባኝ ፡፡ይህ ሁሉ ለዛለለም የሚበቃ ይመስል የነበረው  ደስታ በደቂቃዎች ውስጥ እንዴት እንዲህ  ሊበተን ቻለ……?የትኛው አምላክ ነው እንዲህ በቅጽበት ሰውን ከገነት ወደ ሲኦል አሽቀንጥሮ የሚወረውረው….?ምን አይነት ዕድለቢስነት  ነው…?ምን አይነት መነጠቅ  ምንስ የሚሉት መክሸፍ ነው….. ፡፡

   እኔ ከእሱ ውጭ አኮ እንኳን  ወሲቡ መጋራት ቀርቶ ከንፈር ተሳስሜ አላውቅም…፡፡እሱ እኮ የልቤን ድንግልና…የከንፈሬን ድንግልና ..እና አሁን ደግሞ ቀሪውንም ድንግልናዬን አጠቃሎ ነው የወሰደው…፡፡ ታዲያ የቱ ጋ ነው ችግሩ….?.እኔን እንዴት ሸርሙጣ ሊለኝ ቻለ?ቆይ ግን ክብረ -ንፅህና ማለት ምን ማለት ነው?ራሴን ጠየቅኩ…የእውነት ለእሱ ብቻ እንደተኛው በምን ላረጋግጥለት እችላለው..?አዎ ትዝ አለኝ …ደም፡፡ በፍጥነት ብርድልብሱን ገለጥኩ… አንሶላዎችን አገላበጥኩ……ጠብታ ደም ፍለጋ ሁሉን ነገር አተረማመስኩ …… ፍጽም ንፅህ ነው ፡፡ወለሉ ላይ ቆምኩና የለበስኩትን ቀሚስ ወደ ላይ በመግለብ ጎንበስ ብዬ ብልቴን ፈተሸኩ፤ ዙሪያውን ፍም መስሏአል..የመቁሰል መልክቶችም ይታዩበታል፡፡

ወይኔ ልጅት ምንም የዋሸውት ነገር የለም ፡፡ እስከዛሬ ድንግል ነበርኩ… ሴት የሆንኩት ዛሬ ነው….፡፡አዎ ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት እዚህችው አልጋ ላይ…..፡፡መጮሀ አማረኝ …ማልቃስ አማረኝ ..ዕቃዎችን መሰባበር አማረኝ ..እራሴን ማጥፋት ሁሉ  አማረኝ ..ግን ዝም ብይ አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብዬ አንገቴን ወደ መሬት አቀርቅሬ  ከመነፍረቅ  በስተቀር  ለጊዜው ሌላ ምንም ነገር ለማድረግ አልቻልኩም፡፡እንደታዘዝኩት እንኰዋን  እቤቱን ጥዬ  ለመሄድ  የሚያስችል  እንጥፍጣፊ ብርታት ከሰውነቴ  ማግኘት አልቻልኩም፡፡……ይምጣና  ይግደለኝ…….