መንትያ ልጅ ያላት ተማሪያቸውን ልጅ ተሸክመው ያስተማሩት ፕሮፌሰር

መንትያ ልጅ ያላት ተማሪያቸውን ልጅ ተሸክመው ያስተማሩት ፕሮፌሰር

 በአርጀንቲና መንትያ ልጅ ያላት ተማሪያቸውን ልጅ አዝለው ያስተማሩት መምህር አድናቆት እየተቸራቸው ነው።

ፕሮፌሰር ጆሴ ሉዊስ ኮንቴ በሰሜን ምእራብ አርጀንቲና ታኩማን የሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ዴል ኖርቴ ሳንቶ ቶማስ ዲ አኩዊኖ ነው የሚያስተምሩት።

እናት ማሪያና ኑኔዝ መንትያ ልጆች ያሏት ሲሆን፥ የህጻናት ማቆያ ስፍራ በተፈጠረ ችግር ምክንያት ልጆቿን አስቀምጣ ወደ ትምህረት ቤት የምትሄድበት ስፍራ ታጣለች።

በዚህም የተነሳ እናት ማሪያና ፒስ እና ቶማስ የተባሉ መንትያ ልጆቿን ይዛ ትምሀርት ቤት ለመሄድ ትገደዳለች።

መምህሩ ወደ ክፍል ከመግባታቸው በፊትም ፒስ ማልቀስ ይጀምራል፤ በዚህ ጊዜም አጋዠ ሌክቸረሯ ቀደም ብላ ፒስን ይዛው ትወጣለች።

ከቆይታ በኋላም ቶማስ ማልቀስ ይጀምራል፤ ቶማስ እያለቀሰም ፕሮፌሰር ሉዊስ ወደ ክፍል በመግባት ላይ ነበሩ።

ፕሮፌሰሩ እናት ማሪያና ልጇን በማዘል ትምህሯን እድትከታተል በመፍቀድ፤ የሶሻል ኮሙዩኒኬሽን ትምህርታቸውን ማስተማር ይቀጥላሉ። 

ሆኖም ግን ከግማሽ ሰዓት ቆይታ በኋላ ቶማስን ከእናቱ ላይ ተቀብለው በማዘል ማሪያና ትምህርቷ እንድትከታተል አድርገው ማስተማር ይጀምራሉ።

ፕሮፌሰር ጆሴ ሉዊስ የትምሀር ክፍለ ጊዜው እስኪጠናቀቅ ድረስም ቶማስን አዝለው እያስተማሩ እንደነበረ ነው የሚናገሩት።

የሀገሪቱ ዜጎችም ሁለገብ እውቀት እና ችሎታ ያለው መምሀር በማለት ፕሮፌሰር ጆሴ ሉዊስን በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ላይ በማሞካሸት ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ http://metro.co.uk