‹ ካቲ ካቲ › የሚል ርዕስ ያለው የኬንያ ፊልም ለኦስካር ሽልማት እጩ ሆነ ፡፡

‹ ካቲ ካቲ › የሚል ርዕስ ያለው የኬንያ ፊልም ለኦስካር ሽልማት እጩ ሆነ ፡፡

በህይወትና ከሞት በኋላ ባለ ጭብጥ ላይ የሚያጠንጥን ምናባዊ የኬንያ ፊልም በመጪው ዓመት ለሚካሄደው 90 ኛው የአካዳሚ ( ኦስካር ) ሽልማት በውጭ ቋንቋ የተዘጋጀ ምርጥ ፊልም በሚል ዘርፍ መታጨቱን ዴይሊ ኔሽን ዘገበ ፡፡

የኦስካር ሽልማት መራጭ ኮሚቴ ከካቲ ካቲ በተጨማሪ ኪድናፕድ የሚል ሌላ የኬንያ ፊልም ቢቀርብም የንግግር ቋንቋው በእንግሊዝኛ በመሆኑ መስፈርቱን ሳያሟላ ቀርቷል ፡፡
እንደኮሚቴው መግለጫ ምርጥ የውጭ ቋንቋ ፊልም ለመምረጥ መስፈርቱ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ በተለየ በሌሎች ሃገርኛ መግባቢያዎች መሠራት ይኖርበታል ፡፡

ቀዳሚውን የምርጫ መስፈርት ያሟላው ካቲ ካቲ በአብዛኛው በስዋሂሊ እንዲሁም በሼንግ እና በሌሎች የኬንያ ሃገር በቀል ቋንቋዎች ነው የተሰራው ፡፡

ፊልሙ ለውድድር ከመቅረቡ በፊት በተጨማሪ ማለፍ ያለባቸው ደረጃዎች ይኖሩታል ፡፡
በዚህ መሠረት 90ኛው የአካዳሚ ሽልማት እ.ኤ.አ. መስከረም 23 /2018 በአካዳሚክ ኮሚቴው ይፋ ይደረጋል ፡፡