የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ማርሴሎ ከዚሁ የግብር ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በስፔን መንግስት ባለስልጣናት ክስ ቀርቦበታል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የስፔን ክለቦች እና ተጨዋቾች ስማቸው ከሚነሳበት ተግባር መካከል ቀዳሚው ነው የግብር ማጭበርበር፡፡አሁን ደግሞ የሪያል ማድሪዱ ኮከብ ማርሴሎ ከዚሁ የግብር ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በስፔን መንግስት ባለስልጣናት ክስ ቀርቦበታል፡፡

የ29 አመቱ ብራዚላዊ በአጠቃላይ 490 ሺህ ዩሮ ወይም 576 ሺህ ዶላር በግብር መልክ ለስፔን መንግስት መክፈል ሲጠበቅበት ይህንን አላደረገም በሚል ነው የተከሰሰው፡፡በቀረበው ክስ ላይም በ2007 ሎስ ማሪንጌዎቹን የተቀላቀለው ተከላካዩ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲል ግብር መክፈል አለመፈለጉ ተገልጿል፡፡

ማርሴሎ ክሱን በተመለከተ እስካሁን የሰጠው ምንም አይነት ምላሽ አለመኖሩን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
ከአሁን ቀደም የላሊጋው ፈርጦች ሊዮኔል ሜሲ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ናይማር፣ ዣቪየር ማሸራኖ እና ሌሎችም ተመሳሳይ ክስ እንደቀረበባቸውና ጥፋተኛ በመሆን ቅጣት እንደተላለፈባቸው ይታወሳል፡