ከፓሪሱ ሀብታም ክለብ ጋር ስሙ እየተያያዘ የሚገኘው አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪኒዮ ከክለቡ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው አስታወቀ፡፡

ከፓሪሱ ሀብታም ክለብ ጋር ስሙ እየተያያዘ የሚገኘው አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪኒዮ ከክለቡ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው አስታወቀ፡፡

አሰልጣኙ ከፈረንሳይ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ወደ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን ታቀናለህ ወይ ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ በማንቸስተር የሚያቆየኝን የ5 አመት ኮንትራትም አልፈረምኩም፤ ወደ ፒ.ኤስ.ጂ. አልሄድም ሲል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በቲያትር ኦፍ ድሪምስም አዳዲስ ነገሮችን ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው አሰልጣኙ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ በፊት አሰልጣኙ ልጃቸው ወደ ፈረንሳይ እንዲሄድ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ተከትሎ ነው አሰልጣኝ ሆዜ ስማቸው ከፒ.ኤስ.ጂ ጋር መያያዝ የጀመረው፡፡

ለዚህ ምላሽ አለኝ ያሉት ሞሪኒዮ የእንግሊዝ ሚዲያዎች ከቀናት በፊት በዩናይትድ ለመቆየት ፈረመ አላችሁ አሁን ደግሞ ወደ ፓሪስ ሊያቀና ነው ትላላችሁ ነግር ግን ምንም የተፈጠረ ነገር የለም፡፡ እኔ አሁንም የዩናይትድ አሰልጣኝ ብቻ ነኝ ብለዋል፡፡

አሰልጣኝ ሆዜ ሞሪኒዮ ባለፈው አመት ቀያይ ሰይጣኖቹን የተቀላቀሉ ሲሆን ከአሁን ቀደም ባሰለጠኑባቸው 7 ክለቦች ከ4 አመታት በላይ ቆይታ አልነበራቸውም፡፡