በሸበጥ ጫማ ማራቶን የሮጠው ኢትዮጵያዊ አትሌት አሞኘ ሰንደቁ የውድድሩ አሸነፈ

በሸበጥ ጫማ ማራቶን የሮጠው ኢትዮጵያዊ አትሌት አሞኘ ሰንደቁ የውድድሩ አሸነፈ

ኢትዮጵያዊው አትሌት አሞኘ ሰንደቁ በቻይና በተካሄደ የማራቶን ውድድር ላይ በሸበጥ ጫና ሮጦ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል።

አትሌት አሞኘ በመካከለኛ የቻይና ግዛት በተካሄደው የሶንግሻን ሻዎሊን ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር ላይ ነው በሸበጥ ጫማ ሮጦ ውድድሩን በአንደኝነት ማጠናቀቅ የቻለው።

የማራቶን ውድድሩን ለማጠናቀቅም 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ02 ሰከንድ እንደፈጀበትም ተነግሯል።

በዚህም አሞኘ የ20 ሺህ የቻይና ዩዋን እና የወርቅ ሜዳለሊያ አሸናፊ መሆን ችሏል።

አትሌት አሞኘ ሰንደቁ ከሳምንት በፊት በቻይና ጋንሱ ግዛት ጂጉዋን ዓለም አቀፍ ማራቶን ላይ በመካፈልም በሸበጥ ጫማ ሮጦ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል።

 

ምንጭ፦ People’s Daily, China